የክብረመንግሥት ልጆች እንዴት ተሰባሰቡ?

የመጀመሪያው ጥሪ መቼ ተደረገ?

እነማን መጀመሪያ ወደክብረመንግሥት ሩም ሲመጡ ምን አሉ?

ሁሉም ቀጥሎ ቀርቧል!

Wed Aug 31, 2005 10:58 a.m.

አያልቅበት ሌሊት ሌሊት መኪና ተራ የወጪ ከመጠየቅ በቀር በየቤቱ ልመና አያውቅም ነበር !!የሸዋን መኩዋንንት ስላስቸገረ በእኔ ትዕዛዝ የአዶላን አካፋ እንዲያነሳ ተገደደ ::በሁዋላም አቅሙ እየደከመ ሲመጣ ወደ ክ /መንግስት መጣና የሌሊት ገጣሚ ሆነ ::የሚገርመው በረንዳ አዳሪም ሆኖ አገዛዙን በጣም ይዋጋ ነበር ::
ሰላምታዬ ከያላችሁበት ይድረሳችሁ !!!
This is Ras Biru Woldegabriel.
 ውድ የአዶላ ልጆች ይህቺን ጥሪ ሳቀርብ የክብረመንግሥት ልጆቸ እንድንሰባሰብ በማሰብ ነው
ያቺ እኛን ያስተማረች ት /ቤት አሁን አርጅታ ፈራርሳለች :: ዲፕሎማት ሚኒስትርና ሳይንቲስት ለመሆን የበቁ ታላላቅ ሰዎችን ያፈራች ያቺ ትንሽዋ ራስ ብሩ ወ /ገብርኤል ት /ቤት ዛሬ በአጥንትዋ ቀርታለች ::የዋርካን አምድ ላዘጋጁልን ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለቦሬ ለሻኪሶና ለክ /መንግስት ልጆች ሁሉ ጥሪዬን አቀርባለሁ :: ት /ቤታችንን እናድሳት !!
በመጀመርያ ግን መገናኘቱ አስፈላጊ ነውና : የካምቦ የፈረንጅ ውሀ ,የአራዳ ,የሜጫ ,የኩሚና ;የገበያ ክፍል የኩቾና ሌሎችም ተሰባሰቡ :ተገናኘተን እንኩዋን ትዝታችንን እናውጋ ::
.በሉ በቸር ይግጠመን :: ወዳጃችሁ ራስ ብሩ ነኝ ::

Wed Aug 31, 2005 11:38 am

ወንድሜ /ቴ / ራስብሩ ሰላምታዬ ይድረስህ !ጽሁፍህን ሳነብ ምን እንደተሰማኝ ወዩ ታውቃለች !!ታዲያልህ እዛ 02 ቀበሌ አሰጋኸኝ ወፍጮ ከመድረስህ በፊት ካለችው ድልድይ ጋ ወይም እነ ግርማ ጥንቅሹና እነ ቡጡ እሽቴ ሰፈር የነበሩ አንድ አባት ጦር ሁሌ ክራር ከጃቸው የማይለይ አስታወስካቸው ? እሳቸው በአንድ ወቅት የገጠሙትን ነው ርዕስ ያረኩት .አያልቅበትን አስታውሰዋለሁ ግን ምንም ለማለት አልችልም በጣም ትንሽ ነበርኩ ::ከሀሳብህ ስረዳ The US ወይም Europe ነው ያለኸው : ጅማሬህ እጅግ የሚደነቅ ነው አምላክ ይርዳህ !!ሁላችንም እንድንገናኝ እና እንደችሎታችን ራስ ብሩን ለመርዳት እኔ ቃል እገባለሁ ::አሜሪካን እና አውሮፓ ቢያንስ በስልክ ቅርብ ናቸውና ከሌሎቹም ለመገናኘት ሞክር ::

አደቆርሳ

Wed Aug 31, 2005 2:03 pm

የአባባ እልፍነህ ጉደታን ማሳ የሚያውቅ ቀልቤን ያውቃል !እንዴት ከረማችሁ ክ /መዎች ::የካምቦው ቀልቤ ለጌ ነኝ :ጽሁፎቹን ሳይ በቃ መቼስ ምን ልበላችሁ :አንዴየግራዋ አንዴየወደሬ አንዴ ደሞ የተዋበች መስቀላ ጠጅ በቃ ተጭበረበረብኝ :: አደቆርሳ እኒያ ገጣሚው ሰውዬ 10 አለቃ ጸጋዬ ይባላሉ :: ለሁሉም በመገናኘታችን ደስታዬ ብዙ ነው :
ሰሞኑን በሙሉ ትዝታ እስክንገናኝ ቸር ያቆየን ::

ቀልቤለጌ

Wed Aug 31, 2005 11:15 pm

ወንድሜ ራስ ብሩ ስላምታዬ በአለህበት ይድረስህ ::
አያልቅበትን እኔም ትንሽ ትንሽ አስታውስዋለሁ በደንብ የማስታወስው ወፉን ነው :: ራስ ብሩ ስንቱን አስተምራ እንዲህ መዳከሟ ከልቤ አሳዘነኝ ::እናማ ያስብከው ጥሩ ነው :: ያስተማረችንን ትምህርት ቤት ከወደቀችበት በምንችለው አቅም እናንሳት :: አደቆርሳ መልክት ደርሶኛል አመሰግናለሁ ከጠራአችው ልጆች የማውቀቸው : አልማዝ በርሄን ካናዳ ነው ያለችው :: ጸጋአዛብ ሲዊድን ነው : ተስፉ ለንደን ነው ያለው :: ሰይድ ናጂ የት እንዳለ አላውቅም :: እንዲያውም እህቱ ጓደኛዬ ናት :: በሉ ቸር ይግጠመን የአገር ልጆች

ቅሩንፉድ

Thu Sep 01, 2005 6:35 am

እንዴት ከረማቹ ወገኖቼ !
እናንተን በማግኘቴ መቸም ምን ብዬ እንደምናገር አላቅምምምምም ... ራስ -ብሩን  ቢሉ  አዶላ  አደቆርሳ .. እነዚያ የሚያማምሩ ት /ት ቤቶች .... ደርቀዋልልልልልል
ማርያም መዳህኒያለም ሚካኤል እና ስላሴ ... ጫካቸው ተራቁቶ ከአጂፕ ሆነው ሲያዩት ግርማ ሞገስ የነበረው የማርያም ዳገት አሁን የኔን መላጣ መስሏል ... እረ ጎበዝዝዝዝዝዝዝዝ ... ያንን ሁሉ ዛፍ ጨርሰው ሲያበቁ ራቁቷን አስቀርተው አሁን ወደ ባሌ ተሻግረዋል እነ ጆቫኒ -ጊቢ ዘምባባ አባሎ ሀጂ -ኢብራሂም .. የእንጨት መሰንጠቂያዎች .... አሁን ዝግባ ለስም እንጂ አይታይምምምም
ዶቅማ እንጆሪ አውጥ የሾላ ፍሬ ,, እንደድሮ ወጣ ብሎ መልቀም የለም ...
አሬራ ዳቦሸዌ ወተት ገፉማ ... ስሙ እንጂ የለም አሉኝ ዘመዶቼ ...
ያ የሚያምረው የጉጂ ከንፈር .. ያ በቅቤ እብድድድድድ ያለው አሞጥሙጤ .. ድርቅ መታው አሉኝ .. እረ መቼ ነው ሄጄ የማየውውውው ...
የጋሽ እርሶም ወፍጮ ያሰጋኸኝ የሀጂ -ከድር እና ሌሎቹም ወፍጮ ቤቶች ጦማቸውን ነው የሚያድሩት አሉ .. የሚፈጭ ጠፍቶ ...
መቸም ወፍጮ ቤት ለጠበሳም ቢሆን ... ማስፈጨቱ ቢቀር ለጠበሳም ቢሆን ሳይሄድ የቀረ ያለ አይመስለኝም ... እስኪ ተሰባስበን ስለዛች የወርቅ ሀገር .. ስለዛች የመንግስት ክብር ስለሆነች አገር እናውራ ...

እምምጷ

ባለሱቅ

Thu Sep 01, 2005 7:27 am

ስላም ለናተ ይሁን የወዩ ልጆቸ መቺም እኒ ስለ ክ /መንገስት በተነሳ ቁጥርር እንባዩ ነው የሚቀድመውው ከየት አንስቺ እንደማወራ ባላቅምም እስኪ ከማክስኞና ቅዳሚ ገበያ ልጀምርር የወተት , የቅቢው , የጢፍ , የቦቆሎው , በገናሊ ጉጂ እየተጫነ ክ /መ የሚመጣውው ያ ትልቁ ገበያቸንን በነሱ ተሞልታ እረ ምን ጠፈቶ ክ /መ ጉጁ ወተት ሲያጠጣን በአቡጀዲ ከልሎ አረ ስንቱ ያ ቀይ አፈርር ውይይይ በጣምም ነው ደስስ ያለኝኝ በዋርካ ስር መስባስባቸንን የራስብሩ ( ያዶላ ት /ቢት ) በዛቸ በቀዳዳ አጥር ሽቦ እየሾለክንን የምንገባባት በመጨረሻውው ደወል ደክማለቸ ራስ ብሩ መርዳት አለብንን እኒ በበኩሊ ልረዳ ዝግጅ ነኝ ራስ ብሩ ት /ቢቲንን አስተምራ አሳድጋ ለዚህ ያደረስቸኝ ናትና በሉ ሁላቸንምም በሉ እንበርታ እንግዲህ ከግዚር እርዳታ ጋርር የናተው የወዩ ልጅጅጅጅ ነኝኝኝ

የግልነስ

Fri Sep 02, 2005 4:30 pm

የቋጥኙ ላይ እሬሳ
የዚያ አምበሳ የካሳ
በመቶ አመቱ ቢያገሳ
ስንቱን ስንቱን ቀሰቀሰውሳ " ሰይፉ መታፈሪያ

ወዩ ና ራስ ብሩ እንደመይሳው በመቶ አመታቸው ቢያገሱ ስንቶቻችን ተቀሰቀስን ? ክብረ መንግስት ካመታት በፊት በስራ ሳቢያ ተቀምጬባት ስለነበር ማለፊያ ጽሁፎቻችሁ ባሳብ ይዘውኝ ነጎዱ ::
ቀድሞ ኢሰፓ ጽ /ቤት ከነበረው ወይም ጤና ጣቢያው ፊት ለፊት ካለው (ምናልባት ከነበረው ሆኖ ይሆናል ) ትልቅ የወዩ ዋርካ ስር ጉጂዎች አብዛኛው በእግሩ ከፊሉ በፈረስ ጦር ይዘው የክት ለብሰው አድባሯን በድምቀት ሲዘክሩ ትዝ ይለኛል ::
በቆራዝማ የታጠነ ወተት ቤተልሄም እነ ትእግስት ፍሬ ሆቴል ውስጥ እንጠጣ የነበረው ጣእሙ ዛሬም ይታወሰኛል :: ዙሪያውን የከበበው ደን ካመት አመት ልምላሜ እሚታይበት መልካ ምድር ዛሬም ይደቀንብኛል :: ያ ማራኪ ደን ተመንጥሯል አላችሁ ? አለመታደል ነው :: ያ ከሩቅ እሚሸተው ጉጂዎች እሚለቀለቁት ቅቤም ድሮ ቀረ ? እኒያ የከተሜ ጠረን ሲሸታቸው ሊተናኮሉ እሚቃጡ ከብቶችም ተመናመኑ ?
ኸረ ጎበዝ ጉች ጉች ያለ ጡት ተረሳ ነው እምትሉት ? እንዲያውም በወቅቱ በልጃገረዶቹ ጡት ማራኪነትና ጥጣሬ በጣም በመደመሜ ለጓደኛዬ በጻፍኩት ደብዳቤ ላይ
"አሁን የኔ አሟሟት አሟሟት ነወይ (2)
ጉች ጉች ያለ ጡት አንድ ቀን ሳላይ
እድሜዬን በከንቱ ላጠፋ ነወይ ?" ብሎ ለሚማረረው ድምጻዊ ውብሸት ፍስሀ እድሜው በከንቱ እንዳይባክን ካሰበ ክብረ መ . ብቅ እንዲል ንገረው ብዬው ነበር :: ድምጻዊው ባለበት ወይም ክ . መ . ሄዶ አይኑን ሳያጠግብ ከሆነ ከዚህ አለም የተለየው ያሳዝናል :: ስንቱ ይወሳል ?

የፈረንጅ ውሀን ከቀመሱት አንዱ
አፈ -ጉባኤ

Wed Sep 07, 2005 12:29 pm

በእውነቱ ስለ አዶላ (ክ /መ )በማንሳታችሁ በጣም ደስ ብሎኛል ::የቦሬ ልጅ ብሆንም ክ /መን ከቦሬ ባልተናነሰ እወዳታለሁ : ራስ ብሩም በአንድ ወቅት 7ና 8 ን ዉብሸት ምንድጌ የሚባል ዳይሪክተር በነበረበት ጊዜ ተምሬአለሁ ::በጣም ብዙ ትዝታ አለኝ ሚ /ር ባክስቸር (አሜሪካዊ )አስተማሪ ;ያሽልንግዬ ያሽልንግዬ ጉጂን ጉጂ ጂቤ ገብሬ መላጥዬ : --የሚለው መዝሙር ;በዚያን ጊዜ የነበረ ኳስ (የመሰንጠቂያና ሌሎች ክለቦች ) ወንድሙ ሳንታ ;ሲሳይ ሳንታ ;የወቅቱ አርቲስት አህመድ ሺፋ ;እፍሬም ጎርፉ :ትዝ ይሉኛል ::በተለይ 3ኛው ዙር መሰረተ ትምህርት ዘመቻ ሬጂ እብሮኝ ዘማች የነበረው ጓደኛዬ ወንደሰን ገድሌ ሁሌም አስታውሰዋለሁ ::በተረፈ በርቱ እኔም ት /ቤቴን ለመርዳት ዝግጁ ነኝ ::እዚህ በምኖርበት እንግሊዝ ብዙ ልጆች እንዳሉ አውቃለሁ ::ለማስተባበር በጀምጀም ወዩ ስም ቃልእገባለሁ ::በተለይ ትዝ የሚለኝ ሸዋ ሻይ ቤት በስሙኒ የስጋ ወጥ የምንበላው ;የባላንበራስ መኮንን ሽንኮራ ;የአሮሬሳ ልጆች እነ ካሱ አለማየሁ ና ሌሎች የክ /መ አላዛር ጻዲቅ ;ፍሰሀ ;በተለይ በቀይ ሽብር የተገደለው እሱባለው ሳህሉ ጓደኛዬም ጎረቤቴም ነበር ::የናንተው ወቤ (ጃሎ )

ኢጆሌ ቦሬ ከኢንግሊዝ

ወቤ (ጃሎ )

Thu Sep 08, 2005 2:49 pm

አባ ጮማ ሰፈር ትወልደን አድገን
እነ ወንዱ ጫካን አይተን ቀንትን
ከነ ቦችራ ጋራ ካስ ተጫወትን

ምንም ቢደፈርስ ጎርፍ ቢገባበት
የሳህሉ ውሀ ልብስ ቢታብበት
ያልተጎንጨው ማን አለ ተወልዶ አድጎ ክብረመንግስት

እንደምን ከርማቹሀል የወዩ ልጆት በመጀመሪያ እራሲን ላስተዋውቅ ተወልጂ ያደጉት አዶላ ሲሆን ሰፈሪም አዲሱ ፖስታ በት ወይም የድሮው ቆጭ ሰፈር ነው

አዶላ ወዩ ማህበር በአሚሪካ ስለመመስርቱ ታውካላቹ 15-20 አባል ያለው የሚገውም በቺካጎ ሲሆን እኒም ክመስራቾቹ አንዱ ነን

ሳህሉና አብቱ ኪዳነ የሚኖሩት ቺካጎ ነው

ፖስታቢትሰፈረ

Thu Sep 01, 2005 5:40 pm

መቼም ራስ ብሩ ሲጠራና ቀጥሎ ወዩን በማስከተል ንግግር ሲሞቅ እንኩዋን የተኛውን ቀርቶ የሞተውንም ሳይቀስቅስ የሚቀር አይመስለኝም ::
እንደምን ሰነበታችሁ በማለት ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ ::አዎ እኔም በዚችው ምስኪን ትምህርት ቤት ተምሬ አሁን ያለሁበት ያደረሰቺኝ የራስ ብሩ ው /ገብራኤል ት /ቤትናት ::ሰለሆነም እኔም ለዚች ት /ቤት ባለእዳ ነኝና ከእናንተ ጋር ለመቆም ፈቃደኛ መሆኔን በዚህ አጋጣሚ ልገልጽ ይፈቀድልኝ ::
በተረፈ ራስብሩ :አዶቆርሳ :ቀልቤለጌ :ቅሩንፉድ :ባለሱቅ ና የግልነስ ሁላችሁም ስለ አዶላ ወዩ ስታነሱና ስትጫወቱ እያነበብኩኝ ለተወሰነች ሰከንድ -(ደቂቃም ሊሆን ይችላል ) ሰውነቴ ነው እንጂ እኔ መሀል አራዳ መሀል ቆሜ የማስተውል ሆኜ ነው ያገኝሁት ::ከጥንት ከጠዋቱ ከነ አያልቅበት ና ወፉ ጀምሮ ከዚያም የጋሼ ክብረትን ቅጣት እንዲሁም በጣም የማውቀውን የአባባ እልፍንህን ማሳ አካባቢ ሲነሳ ደግሞ ፍርክርክ ነው ያልኩት ::እኔ ከወጣሁኝ ትንሽ በመቆየቴም ምክንያት ሆኖም ይሆናል ::መቼም እግዜር ብሎ ወዩ እዚህም ብታሰባስበን ና ከጫወታውም ባሻገር ሌላም ቁም ነገሮችንም ለወዩና ለነዋሪው የሚጠቅም መስራት የምንችልበትን በተወያየን በነበር :: እንግዲህ ማሰባሰብ የመጀመሪያ ስራችን ይሁንና ... እንቅጥል ::እዚህም እኔ አካባቢ ፈቃደኝነታቸውን በምጠየቅ ለማሰባሰብ ሞክራለሁ ::

ደህና ቆዩ

ዝምታ

Thu Sep 22, 2005 1:23 pm

እባክቹ ስለ አዶላ ለመልካም ጉዳይ ስታወጉ ምንም አዲስ ብሆንም ለመጻፍ የሀገር ነገር አያስችልም ምን መሰላቹ ስለ ወፉ ስታወጉ ምን ትዝ አለኝ መሰላቹ ወፉ ፍራንክ ስለሚውጥ ሽንቱን የሚሽናበት እንፈልግ ነበር እነ ውብ ጃሎ ባለ ሱቅ ለሎችም ስታወሩ በጣም ነው ደስ ያለኝ በርቱ ብቸኝነቱ አስቸግሮኝ ነበር አሁን እናንተን ሳገኝ ደስ ነው ያለኝ ሰላም ሁኑልኝ 

ቱኩሉ

Posted: Fri Oct 21, 2005 10:14 pm

ሰላምታ ለአዶላ ልጆች

እጅግ በጣም ትዝታ ውስጥ ነው የገባሁት ጽሁፎቻችሁን ሳነብ :: ሰላምታ ከስዊድን ይድረሳችሁ :: በሰፊው ጽሁፌ በሚቀጥለው እንገናኝ :: እጆሌ አዶላ ::

ጉጆ

Posted: Fri Nov 11, 2005 5:45 pm

ታዲአስ አደቆርሳ አንተ ጉደኛ ሊጅ ነህ ,ጸሁፊሂን አየሁት ,ምንም እንኩዋን ባጠገብ ባንገኝም አገራችንን እንናፍቃታለን

ዲዳ

Posted: Sat Nov 12, 2005 6:45

ሰላም ለ አዶላ ልጆች

እንደምን ስንብታችዋል :: አደቆርሳ በምትጽፈው ዽሁፍ በጣም የምተደነቅ ነህ :: ብዙ ትዘታዎች አሉህ : እኔም ክ /መ ተወልጄ በራሰ ብሩ ት /ቤት ተምሬአለሁ ::ነገግን በ አንተና በ ለሎቹ ማለትም ባለሱቅ ,ራሰ በሩ ,የግልነስ , ወ .ዘ .ተ ጊዜ ሳይሆን . ጌታቸው ጅሩ እና በ በተላ በዛብህ ዳርክተር በነበረበት ጊዜ ነበር ::
ለራሰ ብሩ ት /ቤት በማስባችሁ በጣም ይምትደነቁ ናችሁ . አስተዋድዎ ለማድረግ እኔም ዝግጁ ነኝ ::እኔ ያለሁበት ብዙም አይደለንም ግን ያለነውም ለመተባበር ተነጋግረንበታል ::በሉ በደህና ሁኑ ::  

ኩቾ ሠፈር

Posted: Wed Dec 14, 2005 3:43 pm

ሰላም ለሁላቹም

ያገሬ ልጆች ሰላም ለናንተ ይሁን
አዶቆችርሳ ያንተ ነገር በጣም ይገርማል አንዳንዴ በእኔ እድሜ ያለህ ትመስላለህ . ባለፈው ፖስታ ቤት ጥያቄ ጠይቆ ነበር ጥያቄውን ላስታውስክና በ 1976 አ .ም በተካሄደው የስፓርታካየድ ውድድር ላይ ጀምጀምን ወክለው ከሄዱት ስፖርተኞች ዋንጫ ያስገኘው በምን አይነት ውድድር ነው እሱስ ማን ነው መልሱም ፖስታቤት እንደመለሰው ከብሮም (ክብሪት ) ስትሆን እኔም በዛን ጌዜ ተካፋይ ነበርኩኝ .
በእግር ካስ ከተካፈሉት ውስጥ ሙሉጌታ በቀለ ይለማ ተስፋዮ (ካቻማሊ ) ሳውዝ አፍሪካ ነው ያለው አለሜን አህመዴን ወንደሰን ሁሴን ዘውዱ አድማሱ አሜሪካ ነው ያለው አስመሮም ገዳም አሜሪካ ነው ያለው እዮብ ሳፊሳ የ 04 ቀበሌ ልጅ ነው እና ሌሎችም የዋደራ ልጆች .
ሌላው ከሳፍከው ላይ ካገኘውት ይልማና ወንደሰን አዋሳ ላይ ሴጫወቱ ትዝ ይለኛል ብለ ነበር አዚላይ የተሳሳት ይመስለኛል ምክኔያቱም ይልማና ወንደሰን የተጫወቱት የኔ በ 1976 አ .ም ብቻ ነበር ከዚያ ወዲ በካስ አለተገናኙም ምክንያቱም ይልማ ከ 9-12ኛ ክፍል የተማረው ሻሸመኔ ነው .
ሌላው ይልማ 1987 አ .ም ለአዶላ ከነማ እንዴጫወት ተጠርቶ መጥቶ ተጫውታል ግን የተጫወተው ክነ ሌቴ ከነ ቐጂላ ሞገስ አለሚን አህመዲን ማሩፍ አህመዲን አረጋ ዳመና በላቸው ጥበቡ ከይልማ ጋር የተጫወተው የሻኪሶን ለገደቢን ቡድን በመወከል ገንዘብ እየተከፈላቸው ክለቴ ጋር ብቻ ነው እየተመላለሱ የተጫወቱት . በል ቻዎ
የአዶላው ከሳህሉ ውሀ

Posted: Thu Dec 15, 2005 9:04 pm

ትውውቅ

ሰላም ወዩዎች ወበ ጃሎ ተመልካች ብቻ ለምን ትሆናለህ ከዎዩዎች ጋር ተቀላቀል ብሎ ሴሮ እንድጠጣ ስላበቃኝ አመስግነዋለሁ ;;ከ ካልጋሪ ብቅ ያልኩ እጆሌ ቦሬየ ብሆንም አዶላ የትማርኩባት ቤቴ በመሆኑአ እየቆየሁ ቡዙ አዎቹኃለው ;; ስለ ዪልማ ተስፋየ ስለ ዱበ ጂሎ ቁጥሬ ዱለቻ የምላቹ ዪኖራል ;;አዶቆርሳ ስለዎንድራድ መራዊ የምትጽፈው ሁሉ ስራም አላሰራ ብሎኛል ;;ዎቤ ጃሎ እራስህ ብዙ ታሪክ እንዳለህ አውቃለሁና የሰው ብቻ መጻፍ ሳይሆን ባንተም ላይ የምለው አለና ተጠባበቅ ;;ራስ ብሩ ስለታመነ የጻፍከውን ደውየ ነግረው ማንነትህን ደርሶበታል ;;ቦረ ቶሎ የሚመለሰው ቅዳሜና ማክሰኞ ከገበያተኛ ጋር ጠጅ ለመጠጣት እንደሆነ አውቅ ነበር ;;ሌላው ስለታመነ ወቤ ጃሎ የሚያውቀው ታሪክ ስላለ እባክህ ወቤ የፔጆዋን ታሪክ ጀባ በለን ;;ቸር ያሰንብተን ;;

ሞፊቲ ከካናዳ

Posted: Mon Dec 19, 2005 10:32 am

Amazing!!

What the amazing month!!

Couple of weeks ago, one of my friends from Chicago told me about the weyu forum and I checked the site. It is a remarkable one which took me back to my very young age memory. In fact, I was informed about the weyu association of Chicago right after it was over. I wish I new so I would have been meet you guys in Chicago. I dont know why I was not told about the annual meeting, when people even came from DC and California which is far away, where as, I am only 4 hours drive from Chicago. Well, "' Lalefew kiremt bet Ayiseraletim "" I will definitely come on next year meeting.

Two girls who came from DC (ORI and Bisrat) I really admired your commitment. What a wonderful drive. Keep it up!! According to the info I got from the site you were very happy. Man, you make me feel Jealous!! By the way, I am not able to know you, even though my friend tried hard to explain. I think you might not be my batch. But, hey - I know your parents though.

Cheers!!

Aldomoro

Posted: Mon Aug 07, 2006 4:24 am

እናንተ ወዩዎች ቤታችሁ ድምቀቱ
ፍቅራችሁ ሽጋ ነው በዚያ ላይ ውበቱ ......
ስለቁንጅናማ ውበት ከተነሳ
የአዶላ ውበቱ ሁሌም አይረሳ ::

እንግዲህ ዛሬ ቤታችሁ የአዶላ ፍቅር የራስብሩ ትዝታ
አላስቀምጥ ቢለኝ ሆዴን ባር ባር ቢለው እስቲ ቢወጣልኝ ብዬ መጣሁ ::
አዲስ እንግዳ መቼም ማላመድ መቀበል ማስተናገድ ስታውቁበት ለዚህም አይደል እንዴ ስማችሁ ክብረመንግስት .............. መባሉ ::

ድሮ የተማርኩባት ት /ቤቴን ፎቶዋን ሳያት አላስችል ቢለኝ :: በትዝታ ቅውልል ብዬ በሀሳብ በዚያ ግርማ በተሞላው የራስብሩ ጊቢ ከባንዲራው ፊትለፊ ተሰልፌ መዝሙሩን ሳንጰለጵለው ነው የከረምኩት ::

ራስብሩ ተምሮ የሽልንግዬ ትዝታ የሌለው ያለ አይመስለኝም :በዚያ ላይ ሳር ለሳር እየተንፋቀቀ ባገኘው አጋጣሚ ሽልንግዬ ያልቆፈረ ::
እስቲ አውጉን .................

ቸር ይግጠምን ! ውድድድ ነው የማረጋችሁ ::

ሽልንግዬ

Posted: Wed Sep 27, 2006 5:30 pm

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ የክብረ መንግሥት ልጆች
መቼም ይህን አርዕሥት ሳይ ያለ ምንም ማጋነን የልቤ ትርታ ምን ያህል እንደጨመረ ልገልጽላችሁ በቻልኩኝ !

እኔ ራሴ የምኖረው በአሜሪካ ነው እኔም እዚህ በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢየ ካሉ የክብረ መንግሥት ልጆች ጋር ሆነን ላደግንባት ከተማ አንድ ነገር ለማድረግ በማለት በቅርቡ ለመሰብሰብ አቅደናል

ስለዚህ ከናንተ መካከል እዚሁ አካባቢ ካላችሁ ጻፉልኝና እንነጋገራለን

የናንተው ወንድም

አንፈራራ

_________________

Posted: Mon Mar 20, 2006 3:50 am

ሰላም ወዩዎች እንድምን አላችሁ !!! ይቅርታ የአማርናው ክኢቦርድ ስላልተመች ወድ እንግሊዘናው ልዙር , Well, what can i say, when i read your comments, i am totally gutted. I born and grow up in ወዩ i share most of your story and i believe few of you are my childhood friends. Anyway i will be back some other time and comment on the subject. meanwhile i will keep reading. አድቆርሳ you are an amazing guy. your memory serves 100%. ራስ ብሩ , ባለሱቅ , ሁላችሁም you doing very good job and keep up the good work!!

ክብረመንግስት

_________________

Posted: Fri Oct 20, 2006 3:34 pm

ሰላም የክብረ መንግስት እንቁ ልጆች እንደምን አላቹልኝ ? እኔም ክ /መንግስት ያውም የመናህርያ ልጅ ነኝ :: ሁልጊዜ ፅሁፋችሁን እከታተላለው በጣም ደስ ይለኛል ብዙ ነገር እንዲያስታውሰኝ ያደርገኛል :: ይህን ፔጅ ያስተዋወቀኝና ወደዚህ ፔጅ እንድገባ የገፋፋኝን ለቆርቕሪው ለራስ ብሩ ከልብ የሆነ ምስጋና አቀርባለው : LaughingLaughingእንግዲህ ከአሁን በሁላ እሳተፋለው .::የነአንፈራራ ግልነሽ ባለሱቅ አደቆርሳና የራስብሩ የሌሎችም ፅሁፎች አንብቤአለው ደስ ነው ያለኝ በተረፈ አሁን የታሰበውን ሚሽን ልበለው (ስለ ቤተሰብ ላጡ ወገኖቻችን ) በጣም ነው ምደግፈው በማንኛውም ነገር ከጎን አለሁ ::በሚቀጥለው ትዝታዎቼን እፅፋለው በርቱልን :: ቸር ይግጠመን

ክ /መ መናህሪያ