የትውልድ ሀገሬ
አዶላ ልበልሽ ወይስ ክብረ መንግስት
መልካሟ ከተማ ፡ የወርቛ እመቤት
የሻኪሶውን ወርቅ፡ የያዘው ከርስሽ
ክብረመንግስት የሚል : ስም ነው ያስጠሽ
በእውነት ለአገር አንቺ ክብር ነሽ
ወርቅ በያይነቱ ፡ አምርተሽ ሰጥተሽ
እንደው ክብረ መንግስት ፡ አንቺስ ደህና ነሽ?
የአንፈራራን ዳገት ፡ ቁልቁለት ወርጄ
መቼ ነው የማይሽ፡ ወዳአንቺ መጥቼ
የጥጋቡ ዘመን ፡ የቅቤ ወተቱ
እንደምን ይረሳል፡ አዮ ፋዲ ኮቱ
ግንቦት ሰኔ ደርሶ፡ የምንበለው እሸት
ናፍቆቱ መጣብኝ ፡ ትዝ አለኝ በድንገት
በአይነ ህሊናዬ፡ አውጥቼ አውርጄ
በቆየ ትዝታ ፡ በናፍቆት ነጉጄ
በሃገሬ አለማደግ፡ እጅግ ተናድጄ
ማህድኗ ብዙ ፡ እሷ ምስኪን ደሀ
ወርቅ እያፈሰስች እንደወራጅ ውሃ
ክብረ መንግስት ምነው፡ እያደር ማነሷ
ፈጥና እንድትለወጥ ፡ እንድትበለጽግ
ምን ይሆን ብልሃቱ፡ አዶላ እንድታድግ