ልጅነቴ


Grades 1, 2 and 7

መልክተ ዮሃንስ አቡጊዳ ቆጥሬ፣

አባፈለገ ጥሬ በጉንጩን አክብሬ፣

መጠንቆያ ይዤ ፊደል ላይ ቀስሬ፣

የኔታኪዳኔ አባስጢፋኖስጋ ተምሬ፣

ባለንጋቸው ተማርሬ፣

በቁንጥጫቸው አርሬ፣

የፊደል ገበታን ተወጥቼ፣

ዳዊትን በቃል ጠጥቼ፣

ዸዻን ዱኔ፣

ደማን ኛኔ፣

ቁቤ በረኔ፣

ከንሲረቲ ጉደኔ፣፣

እንዴት ልርሳው ልጅነቴን

ግኡዝ አካል እኔነቴን

አንቺ ወዩ አንቺ አዶላ

የልጅነቴ ጥላ

------ይቀጥላል------