ሥላሴ በር ኩቾ ሄጄ፣

ሜጫ ሠፈር ተወድጄ፣

ፈረንጅ ውሃ ተወልጄ፣

ያደኩብሽ ካምቦ ሠፈር፣

መሳለሚያና ኩቾ በር፣

ኮባሶርሳ ቀዩ አፈር፣

ቢሉ ጨፌ አደቆርሳ፣

ጅሪንቲቲ ቡቤ ቆርሳ፣

ገበያክፍል ማርያም ጨፌ፣

ካምቦ ሜዳ ተሰልፌ፣

አራዳ ኳስ ተጫውቼ፣

ድፍን ሽልንግ ተበልቼ፣

ከርክ አሲዤ ተጣልቼ፣

ያደኩብሽ አዶላዬ፣

የትዝታ ከለላዬ፣

ባራት ደብር ባራት አምባ፣

ጸሃይ ወጥታ እስክትገባ፣

ሣቅ ብቻ ነው ሁሌ ደስታ፣

የልጅነቴ ትዝታ……….. ፣፣