ሸራ ጫማ ተጫምቼ፣

በጎርፍ ውሃ ተጫውቼ፣

በጨፌ ወሃ ዋኝቼ፣

መሬት ቆፍሬ ሽልንጋ በልቼ፣

ለቀስት መንች አበጅቼ፣

ሞር ፒንክ ፖንክ ተጫውቼ፣

የካልሲ ኳስ በራፊ ጨርቅ ሠፍቼ፣

እጅ በኪስ ተረትቼ፣

ሹሌ ጥልፊያ ተመትቼ፣

ኩሉሎ ነድቼ፣

ሚዳቋ ድኩላ አደን ወጥቼ፣

ከናጂ ሱቅ ቴምር ከጀማል ቆቆር ገዝቼ፣

ችቦ ለቅሜ ጅራፍ ሠርቼ፣

ቡሄ መጣ ያ መላጣ

ቂቤ ቀቡት ጸጉር ያውጣ

እንዴት ልርሳው ልጅነቴን

ግኡዝ አካል እኔነቴን

አንቺ ወዩ አንቺ አዶላ

የልጅነቴ ጥላ ፣፣